Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

sunbucks

sunbucks

ዜናውን ያሰራጩ

ዜናውን ያሰራጩ!Become an Outreach Partner

የህጻናት የበጋ ኤሌክትሮኒክ ጥቅማጥቅሞች ዝውውር ፕሮግራም (Summer EBT) በመባል የሚታወቀውን SUN Bucks ለማስተዋወቅ እንደ ዲሲ መንግስት የትብብር ጥረቶች አካል፣ እነዚህን የስርጭት መሳሪያዎች እያጋራን ነው።

እነዚህ መሳሪያዎች የ SUN Bucks ጥቅማጥቅሞችን የሚያብራሩ የመረጃ ሉሆችን፣ በራሪ ወረቀቶችን እና የማህበራዊ ሚዲያ ግራፊክሶችን ያካትታሉ። እነዚህ መርጃዎች ቤተሰቦች ስለ አዲሱ ፕሮግራም ማወቃቸውን እና ጥቅማጥቅሞቻቸውን እንዴት እንደሚጠቀሙ መረዳታቸውን ለማረጋገጥ ያግዛሉ።

የስርጭት አጋር ይሁኑ! የስርጭት አጋሮች ዜናው ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች ለማድረስ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። ይህ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፦

  • የአካባቢ የትምህርት ድርጅቶች እና አስተማሪዎች፣
  • የወላች ማህበራት እና ማህበረሰብን መሰረት ያደረጉ ድርጅቶች፣
  • ተሟጋች እና እምነት ላይ የተመሰረቱ ቡድኖች፣
  • የምግብ ባንኮች፣
  • ከትምህርት በኋላ የሚሰጡ ፕሮግራሞች፣
  • እና የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች።

ከዚህ በታች መሳሪያዎን ያግኙ እና ዜናውን በማሰራጨት ይቀላቀሉን!

ለመጀመር እባክዎ የSUN Bucks/ የበጋ EBT ስርጭት እቅድ ማረጋገጫ ዝርዝር ይመልከቱ። 

ዜናውን እንድናሰራጭ ያግዙን እና የ$100 የስጦታ ካርድ ለማሸነፍ ይመዝገቡ!

Help Us Spread the Word

የምንፈልገው ሰው

የዲሲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ወላጆች/አሳዳጊዎች እና የዲሲ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት ተማሪዎች

እንዴት እንደሚሰራ

  1. በሜይ እና በጁን መካከል፣ ለወላጆችዎ እና ጎረቤቶችዎ በሶስት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ መንገዶች ዜናውን ያሰራጩ። ለምሳሌ፣ በወላጅ የኤለኢክትሮኒክ የደብዳቤ ዝርዝር (listservs) ላይ መለጠፍ፣ በወላጅ-መምህር ማህበር (PTA) ስብሰባ ላይ መጥቀስ፣ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ማጋራት፣ በተማሪዎ የመማሪያ ክፍል የ WhatsApp ቡድን ላይ አስተያየት መስጠት፣ ወዘተ።
  2. ያጋሩበትን ቦታ ይቅረጹ ወይም ፎቶ ያንሱ።
  3. ክዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ።

የሚያገኙት ነገር

በእያንዳንዱ ሳምንት፣ ትክክለኛ የተጋሩ ስብስቦችን ያስገባ ሰው ሁሉ እስከ አምስት የሚደርሱ የ$100 ቪዛ የስጦታ ካርዶች ሎተሪ ውስጥ የሚገባ ይሆናል። በአዳዲስ ቦታዎች ማጋራትዎን ከቀጠሉ፣ ብዙ ሳምንታት መግባት ይችላሉ!

በተጨማሪ፣ በአካባቢዎ የሚገኙ ህጻናትን እየረዱ መሆንዎን በማወቅዎ የግል ደስታ ያገኛሉ።

ሎተሪ ውስጥ መግቢያ ቅጽ