ማነው ብቁ የሚሆነው?
ተማሪዎች ለ SUN Bucks ብቁ የሚሆኑት፣ በሚከተሉት ነው፦
- የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የሕዝብ ትምህርት ቤት፣ የዲሲ የሕዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት፣ ወይም በብሔራዊ የትምህርት ቤት ምሳ ፕሮግራም (NSLP) ውስጥ በሚሳተፉ የዲሲ የግል ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ከሆነ፤
- በቅድመ-መዋዕለ-ህጻናት፣ አንደኛ ደረጃ፣ መካከለኛ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመዘገቡ ወይም የጎልማሳ ተማሪ ከሆኑ፤ እና
- ከፌዴራል የድህነት ደረጃ 185 በመቶ ያነሰ ወይም እኩል የሆነ ዓመታዊ ገቢ ባለው ቤተሰብ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ። ለምሳሌ፣ 4 አባላት ላለው ቤተሰብ፣ ያ $57,720 ነው።
ተማሪዎ የሚከተለው ከሆኑ አስቀድሞ ይጸድቅላቸዋል ዕድሜያቸው ከ5 እስከ 18 ዓመት የሆኑ እና ከጁላይ 1፣ 2023 እስከ ማርች 22፣ 2024 ድረስ ተጨማሪ የተመጣጠነ ምግብ እርዳታ ፕሮግራም (SNAP) ወይም ጊዜያዊ እርዳታ ለችግረኛ ቤተሰቦች (TANF) ከተቀበሉ።
SUN Bucks የተዘጋጀው ለምድን ነበር?
ዩናይትድ ስቴትስ በትምህርት አመቱ በUS የግብርና መምሪያ (የUSDA) ትምህርት ቤት ቁርስ እና ምሳ ፕሮግራሞች ለሚሳተፉ 30 ሚሊዮን ለሚሆኑ ተማሪዎች ታቀርባለች። ይሁን እንጂ፣ በበጋ ወራት እነዚህን ጤናማ ምግቦች የማግኘት እድል የሚያጡ አብዛኛዎቹ ተመሳሳይ የሆኑ ተማሪዎች ለምግብ እና ለምግብ ዋስትና እጦት ከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው። በዲሴምበር 2022፣ የሁለትዮሽ ምክርቤት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች ተማሪዎች በበጋ ወራት ተጨማሪ የምግብ ተደራሽነትን ለማቅረብ አዲስ፣ ቋሚ ፕሮግራም አዘጋጅቷል። ይህ ፕሮግራም ተማሪዎች የተመጣጠኑ የትምህርት ቤት ምግቦችን የማግኘት እድላቸው አነስተኛ በሚሆንበት ጊዜ የበጋ የረሃብ ክፍተትን ለመዝጋት የሚያግዝ ይሆናል።