Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

sunbucks

sunbucks

የህዝብ ማስታወቂያዎች

የህዝብ ማስታወቂያዎች

ለተወሰነ የጊዜ ሰሌዳ እውቅና በመስጠት ግዛቶች አዲሱን የበጋ EBT/SUN Bucks ፕሮግራም መተግበር ስላለባቸው፣ የዩናይትድ ስቴትስ የግብርና መምሪያ (USDA) የምግብ እና የአመጋገብ አገልግሎቶች በ2024 የፕሮግራሙን ሙሉ ትግበራ ለመደገፍ ግዛቶች ለመታለፍ እንዲያመለክቱ እየፈቀደ ነው። የበጋ EBT / SUN Bucksን በተሳካ መልኩ በተግባር ላይ ለማዋል፣ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የሚከተሉትን ጨምሮ በርካታ የUSDA መታለፎችን አመልክቷል፦

  • የገቢ ማመልከቻዎች (7CFR 292.12(ረ)(1)) የበጋ EBT ድርጅቱ የተሟላ ማመልከቻ በደረሰው በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ብቁ ለሆነው ልጅ ቤተሰቦች ማሳወቅ (ማስታወቂያ በፖስታ ማስቀመጥ) ይኖርበታል።
    • ዲስትሪክቱ ብቁ የሆኑ ቤተሰቦችን በተቻለ ፍጥነት ያሳውቃል፤ ይሁን እንጂ፣ ግዛቱ የመርጃ ተገኝነትን ለመርዳት ይህንን መታለፍ እየጠየቀ ነው።
  • ውድቅ የተደረጉ ማመልከቻዎች እና የክልከላ ማስታወቂያ 7 CFR 292.12(ሰ) የበጋ EBT ድርጅት የተሟላው ማመልከቻ በደረሰው በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ጥቅማጥቅሞችን ለተከለከለው ለእያንዳንዱ ቤተሰብ የጽሁፍ ማስታወቂያ መስጠት ይኖርበታል።  
    • ዲስትሪክቱ ብቁ የሆኑ ቤተሰቦችን በተቻለ ፍጥነት ያሳውቃል፤ ይሁን እንጂ፣ ግዛቱ የመርጃ ተገኝነትን ለመርዳት ይህንን መታለፍ እየጠየቀ ነው።
  • ጥቅማጥቅም አሰጣጥ 7 CFR 292.15(ሐ)(1)(ሸ)(ሀ)። በመስተጋብር የምስከር ወረቀት ላገኙ ወይም ፋይል ላይ የጸደቀ የበጋ EBT ማመልከቻ ላላቸው ህጻናት የበጋ የስራ ጊዜ ከመጀመሩ ከሠባት እስከ 14 የቀን መቁጠሪያ ቀናት በፊት ጥቃጥቅሞች መሰጠት እና ለተሳታፊዎች መቅረብ አለባቸው።  
    • ዲስትሪክቱ በተቻለ ፍጥነት ጥቅማጥቅሞችን ያሰራጫል፤ ይሁን እንጂ ግዛቱ የመርጃ ተገኝነትን ለማስተናገድ ይህንን መታለፍ እየጠበቀ ነው።
  • የጥቅማጥቅም አሰጣጥ 7 CFR 292.15(ሐ)(1)(ሸ)(ለ) የበጋ የስራ ጊዜ ከጀመረ በኋላ ለሚያመለክቱ ብቁ የሆኑ ህጻናት ጥቅማጥቅሞች ሊሰጡ እና የበጋ EBT ድርጅት የተሟላ ማመልከቻ ከደረሰው በኋላ ከ15 የስራ ቀናት በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ ሊቀርቡ ይገባል። 
    • ዲስትሪክቱ በተቻለ ፍጥነት ጥቅማጥቅሞችን ያሰራጫል፤ ይሁን እንጂ ግዛቱ የመርጃ ተገኝነትን ለማስተናገድ ይህንን መታለፍ እየጠበቀ ነው።

የአድሎአዊነት መግለጫ

ከፌደራል የሲቪል መብቶች ሕግ እና የዩናይትድ ስቴትስ የእርሻ መምሪያ [U.S. Department of Agriculture (USDA)] የሲቪል መብቶች ደንቦች እና ፖሊሲዎች ጋር በተያያዘ፣ ይሄ ተቋም በዘር፣ በቆዳ ቀለም፣ በትውልድ አገር፣ በጾታ (በጾታ ማንነት እና በወሲብ አዝማሚያ ጨምሮ)፣ በአካለስንኩልነት፣ በዕድሜ መሰረት አድሎ እንዳያደርጉ ወይም ከዚህ ቀደም ለተሳተፉበት የሲቪል መብቶች እንቅስቃሴ የተነሳ የበቀል ወይም የአፀፋ እርምጃ እንዳያከናውኑ ይከለክላል።

የፕሮግራሙ መረጃዎች ከእንግሊዘኛ ቋንቋ በተጨማሪ በሌሎች ቋንቋዎች እንዲሰጡ ይደረጋሉ። የፕሮግራሙን መረጃ ለማግኘት የተለየ የመግባቢያ ዘዴ የሚያስፈልጋቸው አካለ ስንኩላን ሰዎች (ለምሳሌ እንደ ብሬል፣ በትልቅ ፊደል ሕትመት፣ የድምጽ ቅጂዎች፣ የአሜሪካ የምልክት ቋንቋ)፣ ፕሮግራሙን የሚያስተዳድሩ የግዛት ወይም የአካባቢው ኤንሲዎች ጋር በመሄድ ወይም ደግሞ የ USDA’ን TARGET ማዕከል በ (202) 720-2600 (በድምጽ እና TTY) ደውለው ማግኘት ወይም በፌደራል ሪሌ ሰርቪስ (Federal Relay Service) (800) 877-8339 በኩል USDA ን ደውለው ማግኘት አለባቸው።

በፕሮግራሙ ላይ የተፈጠረ የአድሎ ሁኔታን አቤቱታ ለማቅረብ፣ ቅሬታ አቅራቢዎቹ የ USDA መርሀግብር የአድሎ አቤቱታ ማቅረቢያ ቅጽ የሆነው ቅጽ AD-3027 መሙላት አለባቸው፣ ቅጹ ኦንላይን በዚህ አገናኝ፦

https://www.fns.usda.gov/sites/default/files/resource-files/ad3027-amharic.pdf

ወይም ከማንኛውም USDA ቢሮ፣ በ (866) 632-9992 ላይ በመደወል፣ ለ USDA የሚላክምደብዳቤ በመፃፍ ማግኘት ይችላል። ደብዳቤው የአቤቱታ አቅራቢውን ስም፣ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር፣ እና ተፈጽሟልምየተባለውን የሲቪል መብቶች ጥሰት ሁኔታ እና ቀን፣ ጉዳዩን የሚመለከተውን የሲቪል መብቶች ምክትል

ሴክረታሪ[Assistant Secretary for Civil Rights (ASCR)] መጥቀስ፣ ተፈጽሟል የተባለውን የአድሎ አሰራር በቂ በሆነም ሁኔታ በዝርዝር ማስፈር አለበት። የተሞላው የ AD-3027 ቅጽ ወይም ደብዳቤ ለ USDA በሚከተለው አድራሻ መቅረብም አለበት፦

  1. በደብዳቤ፦

U.S. Department of Agriculture

Office of the Assistant Secretary for Civil Rights

1400 Independence Avenue, SW

Washington, D.C. 20250-9410; ወይም

  1. ፋክስ፦

(833) 256-1665 ወይም (202) 690-7442፣ ወይም

  1. ኢሜይል፦

[email protected]

    1.  ይሄ ተቋም ሁሉንም ደንበኛ በእኩሌታ የሚመለከት ነው።